Maandag 24 Februarie 2020

ሰበር ዜና

የኦፌኮ ጥያቄ ለምርጫ ቦርድ
                                ------//--------
 ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ
 ጉዳዩ፡ በስልጣን ላይ ባለው ፓርቲ ባለስልጣኖች በአባሎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጫና እንዲወገድልን ስለመጠየቅ ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያውያን በማናቸውም ጊዜ እራሳቸው በመረጡት መንግስት ተዳድረው አያውቁም፡፡ ይህንን ደግሞ ሕሊና ያለው ሰው አይክድም፡፡ ሕዝብ የመረጠው የመንግስት ባለሥልጣን ካለመኖሩ የተነሳ በብረት ኃይል በሕዝብ ጫንቃ ላይ የተፈናጠጡት ባለስልጣናት ሁሉ ጥፋት ሲያጠፉ የገሰፃቸው፣ ወንጀል ሲሰሩ ለሕግ ያቀረባቸውና ከሥልጣን ያወረዳቸው አካል በታሪካችን ውስጥ አልተመዘገበም፡፡ ሕዝብ በመረጠው መንግስት ባለመተዳደራችን የአገራችን ዕድገት ተገትቶ ዝንተ ዓለም የዓለም ጭራና መሳለቂያ ሆነን እንድንኖር ተገድደናል፡፡ ዛሬም ቢሆን ኃላፊነትን የሚወጣ፣ ተጠያቅነትን የሚሸከም እና ግልፅነትን የሚያሰፍን የሕዝብ መንግስት ባለመኖሩ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዕጣ ፋንታ ብሩህ አይደለም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ብዙ ምርምርን የሚጠይቅ ሳይሆን የገዥው ፓርቲ የኢህአዴግ/ብልፅግና ፓርቲ ባለሥልጣኖች ከነበሩበት ፖለቲካ ምህዳሩን የማጥበብ አባዜ ሊላቀቁ አለመቻላቸው ነው፡፡ ለዚህም ጥቂት ማሳያዎችን ለማቅረብ ያህል፡-
1. የገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና ካቢኔዎች በሚፈጥሩት መሰናክል የተነሳ በጂማ ዞን የቅድመ ምርጫ ቅስቀሳ ማካሄድ አልተቻለም፡፡
2. በዚሁ በጂማ ዞን ውስጥ በተፈጠረው ውዥንብር የኦፌኮ አመራርና ሕዝቡ በግንባር መገናኘት አልተቻሉም፤ ወደ ሕዝብ ቀርበን ጉዳያችንን እንዳናስረዳ ለመንግስት ተቋማት የፃፍናቸውን ደብዳቤዎች የተቋማቱ ኃላፊዎች አንቀበልም በማለት ብዙ ካጉላሉን በኋላ  ፈርመው የተቀበሉበትንም ቅጂ ቀምተው ቀዳደው በመጣል ዋናውን ወርውረው ጥለዋል፡፡
3. ለማንኛውም ሕጋዊና የተፈጥሮ ሰው ካለወገንተኝነት አገልግሎት መስጠት ያለበት የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር የመሰብሰቢያ ስፍራ ከልክሏል፤  ከብዙ ውጣውረድ በኋላ የፈቀደውን የስብሰባ መግቢያ መንገድ በአፈር ዘግቷል፡፡
4. በሲቪል መተዳደር ያለባቸው የመንግስት መዋቅሮች በአራቱም የወለጋ ዞኖች፣ በሁለቱም ጉጂ ዞኖችና ሌሎች አዋሳኝ ዞኖችና ክልሎች ከወታደራዊ ኮማንድ ፖስት ሥር እንዲወድቁ ስለተደረጉ አባሎቻችን በሚገባ መንቀሳቀስ አልቻሉም፡፡
5. የኦፌኮ ቢሮዎች አንድም አመራሮችን በማሰር አልፎ አልፎ ደግም ጨርሶም በመዝጋት (ምዕራብ ወለጋ ግምቢ) እና በሌሎች ቦታዎች ደግሞ አመራሮችን በማስፈራራት (ጉጂ) ችግር ላይ በመውደቃችን የአባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን ሕልውና አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መግባቱ ብቻ ሳይሆን በምርጫው ሂደት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡
6. ነገ ለምርጫ ቢቀርቡ ተወዳዳሪ ይሆናሉ የሚባሉ አባሎቻችን በስፋት እየታሰሩ ይገኛሉ፡፡
6.1. አቶ አብርሃም ድአኖ የምዕራብ ወለጋ ዞን ኦፌኮ ኮሚቴ ምክትል አስተባባሪ ታስሯል፣
6.2. አቶ ሞሲሳ ሽፈራ ከምስራቅ ወለጋ ዞን ሐሮ ሊሙ ወረዳ በተደጋጋሚ ታስሮ አሁንም እስር ላይ ይገኛል፤
6.3. አቶ ኃይሌ ሰለሞን ከነቀምቴ ከተማ መታሰር ብቻ ሳይሆን ደካማ ብልታቸው ላይ በመረገጣቸው አካላቸው ይደማል፡፡
6.4. አቶ ጃታኒ ምትኩ የኦፌኮ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የምዕራብ ጉጂ ኦፌኮ ኮሚቴ ፀሐፊ፤ ከዚህ ቀደም በጦላይ ለስድስት በሰንቀሌ ለሦስት ወራት አሁን ደግሞ ለ3ኛ ጊዜ ታስረው ይገኛሉ፡፡

6.5. ወጣት ዱጎምሳ ነጋሳ ሰሜን ሸዋ ዞን ወጣት ሊግ አስተባባሪ
6.6. አቶ በሽር መሐመድ ከአርሲ ዞን
6.7. አቶ ድንቁ መንግስቱ ከአርሲ ዞን
6.8. አቶ ጀማል ጃዋር ከአርሲ ዞን
6.9. አቶ ኑራ አብደላ ከአርሲ ዞን
6.10. አቶ ራማዳን አብዱልቃድር ከአርሲ ዞን
6.11. አቶ ዋጩ ዱባ ከምዕራብ ጉጂ ዞን
6.12. አቶ ገመቹ አና ከምዕራብ ጉጂ ዞን
6.13. አቶ ትሴ ጃርሶ ከጉጂ ዞን
6.14. አቶ ሊባን ገናሌ ከጉጂ ዞን
6.15. ወጣት ሞርካ ቶለሳ የሰበታ ሐዋስ ኦፌኮ ወጣት ሊግ አስተባባሪ
6.16. አቶ አህመድ ኑር ከሰባታ ሐዋስ
6.17. አቶ አበቤ ዲሳሳ ከሰባታ ሐዋስ
6.18. አቶ አዲሱ ዲሳሳ ከሰባታ ሐዋስ
6.19. አቶ አብዲ ኤባኑ ከሰባታ ሐዋስ
6.20. አቶ ራቢራ ዳባሬ ከሰባታ ሐዋስ
6.21. አቶ አበራ በቀለ ከሰባታ ሐዋስ
6.22. አቶ ደበላ ቢራቱ ከሰባታ ሐዋስ
6.23. አቶ ታምሪ አላማየሁ ከምዕራብ ሸዋ
6.24. አቶ በቀለ ጎሹ ከምዕራብ ሸዋ
6.25. አቶ አዱኛ ብርሃኑ ከምዕራብ ሸዋ
6.26. አቶ ተፈሪ ገቢሳ ከቀሌም ወለጋ ዞን
6.27. አብዲ ብርሃኑ ተሰማ ከምዕራብ ወለጋ
6.28. አብዱልከርም አደም ገመቹ
6.29. አብርሃም ፍቃዱ አብዲሳ
6.30. አጎናፍር ካሴ ጥላዬ
6.31. አድነዉ በየነ
6.32. ቢቅላ ማሞ ዱፈራ
6.33. ቢያ ጥላሁን
6.34. ናስር ዮናስ ደረሳ
6.35. ወንዳየሁ አለማየሁ ለገሰ
6.36. ዮናስ አስፋዉ ሰንበቴ
6.37. ቀኖ አበራ ሊካሳ
6.38. ዋቅጅራ ተዘራ ቡልቻ
6.39. ተክለ ተመስገን ቱቾ
6.40. ፍሮምሳ በላቸዉ
6.41. ታጁ አባ ጅሃድ
6.42. ኤባ ግርማ
6.43. ወንዳየሁ አለማየሁ ለገሰ
6.44. ዋቅጋሪ ሞቲ
6.45. ተፈሪ ዋቅቶላ
6.46. ራማታ ከማል
6.47. ታሪኩ ኢማና
6.48. ታሪኩ አብዲሳ
6.49. ታሪኩ ደጀኔ
6.50. ጫላ አበራ
6.51. ዳንኤል ቢራቱ
6.52. ደበላ ቢራቱ
6.53. በቀለ ዋቅጅራ
6.54. ተመስገን አበራ
6.55. መዝገቡ ተስፋ
6.56. አማኑኤል በንቲ
6.57. ልጃለም አለማየሁ
6.58. ኬኒያ ብርሃኑ
6.59. ደረጀ ቡልቲ
6.60. በላይ አብደታ
6.61. ቡልቲ ተመስገን
6.62. ዘምባባ ባጫ
6.63. አማኑኤል ቡልቲ
6.64. አለማየሁ ለሜሳ
6.65. ደገፋ በየነ
6.66. ሰለሞን ደሜ
6.67. ፀጋዬ ታፈሰ
6.68. ኃይሉ ነገራ

6.69. ጉተማ ገላልቻ ከምዕራብ ሐረርጌ ናቸዉ፡፡
7. እነዚህ ዜጎች በተደጋጋሚና በጅምላ ከመታሰራቸውም በላይ ለሕግ አካል አልቀረቡም፡፡ የሕግ የበላይነትና ወሳኝነት አብቅቶለታል ለማለት ከሚቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሶዋል፡፡
8. አንዳንድ ዞኖች ውስጥ ዜጎች ከመደበኛ እስር ቤት ውጭ ለምሳሌ ነቀምቴ የቀድሞው ደጃዝማች ኩምሳ ሞረዳ ቤተ መንገግስት ውስጥ ለረጅም ጊዜ ታስረዋል፡፡ ሌላው የእስሩ ቦታ አሳሳቢነትን አሰመልክቶ ሞቃት የአየር ንብረት ወዳለበት አከባቢ ለምሳሌ አዋሽ አርባ ወደ መሳሰሉት አከባቢዎች እየተጋዙ ይታሰራሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት የጠላትነት ስሜት የማያባራ ከሆነ የተለያዩ ግጭቶች ሊነሱ ይችላሉ የሚል ስጋት አለን፡፡
9. በአማራ ክልል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ስለተገደሉት የኦሮሞ ተማሪዎች የተባለ አንዳች ነገር የለም፡፡
10. አራቱ የወለጋ ዞኖችና ሁለቱ የጉጂ ዞኖች እንዲሁም ሌሎች አዋሳኝ ዞኖችና ክልሎች በወታደራዊ ኮማንድ ፖስት ሥር በመሆናቸዉ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና በቦርዱ መመሪያ ቁጥር 3/2012 መሰረት የኦፌኮ መስራች አባላትን መዝገቦ መጨረስ አልተቻለም፡፡
11. እነዚህና ለመዘርዘር የሚያስቸግሩ ሁኔታዎች እያሉ እንዴት ተደርጎ ምርጫ እንደሚካሄድ እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንደሚደረግ ቦርዱ አቅጣጫ ያስቀምጣል ብለን እንጠብቃለን፡፡
ስለዚህ፤ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ወቅታዊና አስፈላጊ የእርምት እርምጃ እንዲወስድልን እየጠየቅን፤ የእርምት እርምጃው ካልተወሰደ  በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው ችግር፣ እየተከሰተ ያለው ሕገወጥነት፣ እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የዜጎች በሰላም ውሎ መግባት አለመቻልና እና የመሳሰሉ ችግሮች የምርጫውን ሂደት ችግር ውስጥ መክተታቸውንና ቦርዱም ለዚህ ችግር መፍትሄ ለመስጠት  አለመፈለጉን ለህዝብ ለመግለጽ የምንገደድ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡
ከበጎ ሰላምታ ጋር!

በቀለ ገርባ
የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር
via Abdisa Bancha Jara

Geen opmerkings nie:

Plaas 'n opmerking

GMN/lOTOONNI PP WBO-TTI MKAMAN