የእሬቻን በዓል ለማደናቀፍ ሊውሉ የነበሩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የእሬቻን በዓል ለማደናቀፍ ሊውሉ የነበሩ የጦር መሳሪያዎችና ቦምቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ ለሚከበረው የእሬቻ በዓል ያደረገውን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።
ኮሚሽኑ በመግለጫው የእሬቻን በዓል ለማደናቀፍ፣ የተለያዩ አካላት የራሳቸውን አጀንዳ ለመስፈጸም እና ለጥፋት ሊጠቀሙባቸው የነበሩ የጦር መሳሪያዎችና ቦንምቦች ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ ሲሉ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።
የጦር መሳሪያዎቹን ለማስገባት ሲሞክሩ የነበሩ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽኑ በመግለጫው አመላክቷል።
በሌላ በኩል የበዓሉ ታዳሚዎች የእሬቻ በዓል ከሚፈቅዳቸው ስነ ስረዓቶች ውጪ ግጭት የሚቀሰቅሱ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎችን ከማድረግ እንዲሁም የማህበረሰቡን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶችን ከመፈፀም እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
የእሬቻ በዓል አዘጋጆች፣ ኮሚቴዎች፣ ፎሌዎች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ፣የአዲስ አበባ ወጣቶችና የወጣቶች ፌዴሬሽን ፖሊስ ያወጣውን መመሪያ ግምት ውስጥ በማስገባት በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል።
የበዓሉ ተሳታፊዎች በዓሉን ሲያከብሩ የተለየ እንቅስቃሴ ሲመለከቱ በአካባቢው ለሚገኝ ፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጡም ኮሚሽኑ አሳስቧል።
በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ስጋት በሳም እንዲከበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የገለጸው ኮሚሽኑ ፥በዓሉ የፍቅር፣ የአንድነትና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
Geen opmerkings nie:
Plaas 'n opmerking