የአብይ አህመድ ነጭ ውሸቶች ውርደት
ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ወደ እንግሊዝ ሃገር ሲሰደዱ እንደንጉስ አቀባበል ተደርጎላቸው ተስተናግደዋል የሚለው የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የዛሬው የሚዲያ ዲስኩር ትክክል እንዳልሆነ በጉዳዩ ላይ ጥቂት የታሪክ ንባብ ያለው ሁላ የሚገነዘበው ነው —ነጭ ውሸት ነው ላለማለት 🙂
ንጉሱ ማይጨው ላይ ጦራቸው በጣሊያኖች ተሸንፎ ወዳመጣለት ከተበተነ በኋላ እርሳቸውና ቤተሰቦቻቸው ወደ እንግሊዝ ሃገር ሲሸሹ፣ የእንግሊዝ መንግስት እንደ ተራ ስደተኛ ተቀብሏቸው ሲያበቃ፣ Bath በምትባል የኢንግላንድ ትንሽዬ ከተማ ውስጥ መኖሪያ ቤት በመስጠት በወቅቱ ለማንኛውም ተራ የፖለቲካ ስደተኛ የሚሰጥ ሃያ ፓውንድ ሳምንታዊ ድርጎ እየከፈላቸው አጤ ሃይለስላሴን ለአምስት ዓመታት እንዳኖራቸው በዘመናዊት ኢትዮጵያ political history ላይ ለረጅም ዘመናት ጥናት ያደረጉትና መጽሃፍትን የጻፉት እንግሊዛዊው መሪ አፍቃሬ-ኢትዮጵያ ምሁር (authoritative Ethiopianist scholar) ፕሮፌሰር ክላፋምን ጨምሮ በርካታ የውጭና የሃገር ውስጥ ምሁራን በየጽሁፎቻቸው የገለጹት ነገር ነው።
—-
ማሳካት የምትፈልገውን የቤተ-መንግስት ህንጻ እድሳትና ግንባታ ፕሮጄክት አይዲያ ለመሸጥ ሲባል ብቻ በሰፊው የሚታወቅ የታሪክ እውነታን አጣሞ ማቅረብ ትክክል መሆን የሚችል አይመስለኝም። ተቀባይነትም የለውም ...ትርፉም ትዝብት ብቻ ነው።
የኢትዮጵያ ብዙዎቹ ህዝቦችም ሆኑ በጦር ሜዳ ሽንፈቱ ምክኒያት ሸሽቶ በስደተኝነት የተጠለለባት ኢንግሊዝ “ታላቅ ንጉስ” ያላሉትን አጤ ሃይለስላሴ, በተራ ውሸት ላይ በመሞርከዝ “ተሰዶ እንኳን እንደ ንጉስ አቀባበል የተደረገለት መሪ ነበረን” ማለት ተራ ቅጥፈት እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል?
#Ethiopia
Geen opmerkings nie:
Plaas 'n opmerking